የሩዋንዳ መከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች ልዑክ ቡድን የኢትዮጵያ መከላከያ ተቋማትን ጎበኘ

You are currently viewing የሩዋንዳ መከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች ልዑክ ቡድን የኢትዮጵያ መከላከያ ተቋማትን ጎበኘ

AMN – መጋቢት 6/2017 ዓ.ም

የሩዋንዳ መከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች ልዑክ የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪን እና የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲን ጎብኝቷል።

ልዑኩ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ሲደረስ የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ኃይለማርያም አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

በመከላከያ ዩኒቨርስቲም የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ መኮንኖች አቀባበል ማድረጋቸውን ከመከላከያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የየተቋማቱ አመራሮችም ለሩዋንዳ ከፍተኛ መኮንኖች ልዑክ የየክፍሎቹን ስራዎች በተመለከተ ገለፃ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የሩዋንዳ ከፍተኛ መኮንኖች ልዑክ የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲን የተለያዩ ክፍሎች ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንጅነሪግ ኢንዱስትሪ እና የመከላከያ ዩኒቨርስቲ የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት የሚያሳዩ ስጦታዎችን ለልዑኩ ስጦታ ያበረከቱ ሲሆን፣ የሩዋንዳ መከላከያ ልዑካን ቡድንም ለሁለቱ የመከላከያ ተቋማት ስጦታ ማበርከቱ ተገልጿል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review