AMN – ጥር 22/2017 ዓ.ም
የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር ፓርቲ ዋና ጸሃፊ ዌላርስ ጋሳማጌራ የአንድነት ፓርክን ጎብኝተዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሐሳብ ከጥር 23 እስከ 25 በአዲስ አበባ ያካሂዳል።
በጉባኤው የሚታደሙ የውጭ ሀገራት የገዥ ፓርቲ ተወካዮች አዲስ አበባ በመግባት ላይ ይገኛሉ።
የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር ፓርቲ ዋና ጸሃፊ ዌላርስ ጋሳማጌራ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ለመታደም በትላንትናው እለት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ዋና ጸሃፊው በዛሬው እለት የአንድነት ፓርክን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን፤ በፓርኩ አስጎብኚዎችም ገለጻ እና ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል።
የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር ፓርቲ ዋና ጸሃፊ ዌላርስ ጋሳማጌራ በትላንትናው እለት አዲስ አበባ ሲገቡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቱሪዝም ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል እንዳደረጉላቸው እንደሚታወስ ኢዜአ ዘግቧል።