የራስን ስልጣን ለማስቀጠል የሚደረግ የጦርነት ቅስቀሳ በትግራይ ህዝበ ተቀባይነት የለውም- ዶክተር አረጋዊ በርሄ

You are currently viewing የራስን ስልጣን ለማስቀጠል የሚደረግ የጦርነት ቅስቀሳ በትግራይ ህዝበ ተቀባይነት የለውም- ዶክተር አረጋዊ በርሄ

AMN- መጋቢት 8/2017 ዓ.ም

የራስን ስልጣን ለማስቀጠል የሚደረግ የጦርነት ቅስቀሳ በትግራይ ህዝብ ተቀባይነት የለውም ሲሉ የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፖርቲ ሊቀመንበር አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ተናገሩ።

አሁን ላይ በህወሀት አመራር እየተፈጸመ ያለው ድርጊት ክልልሉን አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ መክተቱን ዶክተር አረጋዊ ገልጸዋል።

ላለፋት 3 አሥርት ዓመታት በህውሀት አገዛዝ ስር ለነበረው የትግራይ ህዝብ እውነታው የተደበቀ አይደለም ያሉት ዶክተር አረጋዊ፣ አሁንም የህውሀት አባላት ሽኩቻ የስልጣን እና የሀብት ጥያቄን የመመለስ እንጂ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አለመሆኑን ተናግረዋል።

በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ፖለቲካ ፖርቲዎች በክልሉ በነጻነት የመንቀሳቀስ መብታቸው ተነፍጓል ያሉ ሲሆን፣ የትግራይ ህዝብ ከዚህ ሰቆቃ እንዲላቀቅ መንግስት በትኩረት መስራት አለበት ብለዋል።

ትግራይ ክልል የኢትዮጵያ አንድ ክልል እንደመሆኑ መጠን በስልጣን ጥመኞች ፈተና ውስጥ መግባት ስለሌበት፣ እንደሀገር ለክልሉ አሁናዊ ሁኔታ ትኩረት ሊሰጥበት ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

በሂሩት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review