የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፖፕ ፍራንሲስ ዕለተ ቀብርን ለመወሰን ካርዲናሎች በዛሬው ዕለት በቫቲካን እንደሚመክሩ ተገልጿል።
ፖፕ ፍራንሲስ በትናንትናው ዕለት በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ቫቲካን ማስታወቋ ይታወሳል።
ቫቲካን በመግለጫዋ ፖፑ ከባድ ስትሮክ እና ሊመለስ የማይችል የልብ ችግር አጋጥሟቸው እንደነበር ይፋ አድርጋለች።
የሊቀ ጳጳሱ ሞት በዓለም ዙሪያ ባሉ የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ከባድ ሐዘን ፈጥሯል።
የፖፕ ፍራንሲስን ህልፈት ተከትሎ ቤተ ክርስቲያኗ በቀጣይ ሳምንታት አዲስ መሪ እንደምትመርጥ እንደሚጠበቅም ቢቢሲ ዘግቧል።