የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ኮር ለህገወጥ ቡድኑ ሎጀስቲካዊ አቅርቦት ሊውል የነበረን ተተኳሽ በቁጥጥር ስር አዋለ

AMN- ታኅሣስ 26/ 2017 ዓ.ም

የኮሩ ዘመቻ ሀላፊ ሻለቃ መላኩ ቶላ በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ ለህገወጥ ቡድኑ ሊደርስ የነበረ በርካታ ተተኳሽ በታርጋ ቁጥር 07113 አማ በሆነ ባጃጅ ለሁከት እና ግርግር ተልዕኮ እንዲውል ሲዘዋወር ሠራዊቱ ከማህበረሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሠረት በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልፀዋል ።

እንደ ሻለቃ መላኩ ቶላ ገለፃ ቀጠናው ህገወጥ የመሳሪያ ዝውውር የተበራከተበት እንደመሆኑ መጠን ቡድኑ ይህንን በመጠቀም በተደጋጋሚ በርካታ የጦር መሳሪያ እና ተተኳሽ ለማዘዋወር ቢሞክርም ሠራዊቱ በሚያደርገው ጥብቅ የመረጃ ክትትል ተልዕኮውን ማክሸፍ ተችሏል ።

ነዋሪነታቸው በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ ገራዶ ቀበሌ የሆኑት አቶ አወል መሀመድ፣አቶ እሸቱ ይማም እና አቶ አወቀ አራጋው ለፅንፈኛ ቡድኑ የሎጀስቲካዊ አቅርቦት የሚውል የዲሽቃ ጥይት ለማዘዋወር ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ግለሰቦቹ ከዚህ ቀደምም ለቡድኑ የጦር መሳሪያና ተተኳሽ ሽያጭን ሲያቀነባብሩ እና ሲያዘዋውሩ የነበረ መሆኑ መገለጹን ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ የትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።

ትጥቁ ለህገወጥ ቡድኑ ደርሶ ለሞት ፣መፈናቀል እና ንብረት ውድመት ከመዳረጉ በፊት በሠራዊቱ ቁርጠኝነት እና በህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ሥር የዋለ ሲሆን ለዚህም የአካባቢው ማህበረሰብ እያደረገ ያለውን የማያቋርጥ ድጋፍ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

All reactions:

6767

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review