የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች በመንግሥትና በግል ባለሃብቱ የማይሸፈኑ የልማት ሥራዎችን በመተካት ወሳኝ ሚና እየተወጡ ይገኛሉ- አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

You are currently viewing የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች በመንግሥትና በግል ባለሃብቱ የማይሸፈኑ የልማት ሥራዎችን በመተካት ወሳኝ ሚና እየተወጡ ይገኛሉ- አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

AMN – ጥር 6/2017 ዓ.ም

የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ከለውጡ በኋላ በመንግሥትና በግል ባለሃብቱ የማይሸፈኑ የልማት ሥራዎችን በመተካት ወሳኝ ሚና እየተወጡ እንደሚገኙ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ፡፡

12ኛው የኢፌዲሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና የክልልና የፌደራል ባለድርሻ አካላት የጋራ ጉባኤ በጋምቤላ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር እንደገለጹት፣ መንግስት በርካታ ፈተናዎችን እያለፈ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከለውጡ በኋላ በመንግሥትና በግል ባለሃብቱ የማይሸፈኑ የልማት ሥራዎችን በመተካት ወሳኝ ሚና እየተወጡ እንደሚገኙ አብራርተዋል።

ሲቪል ማህበረሰብ በሀገሪቱ ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን መፍታት እንዲችሉ ህግና ፖሊሲዎችን አዘጋጅቶ በነፃነት እንዲንቀሳቀሱና መብቶቻቸው እንዲከበሩ አድርጓል ነው ያሉት።

ሲቪል ማህበረሰቡ ለኢትዮጵያ ልማት እና ሰላም ግንባታ በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩ መንግስት የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አፈ-ጉባኤው አስታውቀዋል።

የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጋትሉዋክ ሮን በበኩላቸው፣ የሲቪል ማህበረሰብ በሀገሪቱ ተመዝግበው በልማት፣ በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ፣ በሰላም ግንባታ፣ በሰብዓዊ ድጋፍ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በስፋት መንቀሳቀስ የሚችሉበት አውድ መፍጠር ተችሏል ብለዋል።

ሲቪል ማህበረሰብ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ እና በዘርፉ የተጀመሩ ሪፎርሞች መሰረት እንዲይዙ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።

በቀጣይም የሲቪል ማህበረሰብ ምክር ቤትን ጨምሮ ህግን አክብረው የሚሰሩ ሲቪል ማህበረሰብ ሁሉ ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ ጥሪ ማቅረባቸውን ከጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review