የሲቪል ምዝገባና ስታትስቲክስ መረጃን በመላ ሀገሪቱ ወጥ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው-የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት

You are currently viewing የሲቪል ምዝገባና ስታትስቲክስ መረጃን በመላ ሀገሪቱ ወጥ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው-የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት

AMN-ጥር 15/2017 ዓ.ም

የሲቪል ምዝገባና ስታትስቲክስ መረጃን በመላ ሀገሪቱ ወጥ ለማድረግ የቴክኖሎጂ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ገልፀዋል።

በዋና ዳይሬክተሯ የተመራ የተቋሙ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ልዑክ በታይላንድ የሲቪል ምዝገባና ስታቲስቲክስን ከሚመሩ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር የልምድ ልውውጥና ምክክር አድርጓል።

በዚህ ወቅትም ታይላንድ በዘርፉ ያላትን ምርጥ ተሞክሮ ፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና አተገባበር ላይ ያስመዘገበችውን ስኬት፣ ያጋጠማትን ተግዳሮትና ፈተናዎችን የተወጣችበት መንገድ በሚመለከት ገለፃ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

በልምድ ልውውጡ ወቅት የወሳኝ ኩነት የሆኑ የሞት፣ ልደት፣ ጋብቻና ፍቺ መረጃዎችን በተገቢው መልኩ መዝግቦ መያዝ በተለይ ለማደግ እየተጋች ለምትገኝ ሀገር ወሳኝ ነው ብለዋል ዋና ዳይሬክተሯ፡፡

በታይላንድ ከተዘረጋው የቴክኖሎጂ ስርዓት ውስጥ ለኢትዮጵያ የሚሆኑ ጠቃሚ ልምዶችን እንደቀሰሙም ጠቁመዋል።

ታይላንድ ተግባራዊ ያደረገችው የቴክኖሎጂ ስርዓት ከመረጃ አያያዝ ባሻገር ተቋሙን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በማስተሳሰር ወሳኝና አስፈላጊ የመረጃ ልውውጥ በተገቢው ጊዜ እንዲከናወን ያገዘ መሆኑንም መናገራቸውን ከኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review