AMN- የካቲት 7/2017 ዓ.ም
የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በተለያዩ የክልል ከተሞች አራት የአይነ-ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችል የድጋፍ ስምምነት ከተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የካሊፍ ቢን ዛይድ አል-ናሃያን ፋውንዴሽን ጋር ተፈራርሟል፡፡
ስምምነቱን ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውና እና የፋውንዴሽኑ ዳይሬክተር ጀነራል ሙሃመድ ሃጂ አልከሆሪ ተፈራርመዋል፡፡
የካሊፋ ቢን ዛይድ አል-ናሃያን ፋውንዴሽን በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ ተመርቆ ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ተወጣጥተው የመጡ አይነስውራን ተማሪዎችን በማስተማር ላይ የሚገኘውን ብርሀን የአይነ-ስውራን 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት በመገንባት ድጋፍ ማድረጉን ፅህፈት ቤቱ በመረጃው አስታውሷል፡፡