የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት በማድረግ ወደ ሥራ መግባቱን የፀጥታ ጥምር ኃይል ገለፀ

You are currently viewing የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት በማድረግ ወደ ሥራ መግባቱን የፀጥታ ጥምር ኃይል ገለፀ

AMN – ታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሠራዊት፤ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፤ የኦሮሚያ ፖሊስ፣ የድሬዳዋ ፖሊስ እና የሐረሪ ፖሊስ በጋራ በመቀናጀት ታኅሣሥ 19 በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ሜታ ወረዳ የሚከበረው የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት በማድረግ ወደ ሥራ መግባታቸውን ገልፀዋል።

የፀጥታ ጥምር ኃይሉ በኦሮሚያ ክልል የምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች እንዲሁም ከምስራቅ ሸዋ ዞን ጀምሮ በአካባቢው አሰሳ እና በዋና ዋና መንገዶች ፍተሻ በማድረግ ከአስተዳደር አካላት፣ ከሃይማኖት አባቶች እና ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመተባበር ታዳሚዎች በዓሉን በሰላም አክብረው እንዲመለሱ አስተማማኝ የፀጥታ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል።

የክብረ በዓሉ ታዳሚዎችን የሚያጓጉዙ አሽከርካሪዎች የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰት ሕግን በማክበር በኃላፊነት ማሽከርከር እንዳለባቸውም የጥምር ፀጥታ ኃይሉ አሳስቧል።

የአካባቢው ሕብረተሰብ የተለመደ የእንግዳ ተቀባይነት ባህሉን በማሳየት ለእንግዶች አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግና ለፀጥታ ስጋት የሚሆኑ ሁኔታዎችን ሲመለከት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (EFPApp) በመጠቀም ወይም በነፃ የስልክ መስመር 991 በመደወል ጥቆማ በመስጠት ወይም መረጃውን በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት በአካል እንዲያደርስ ጥምር የፀጥታ ኃይሉ ጥሪውን ማቅረቡን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review