በካናዳ እየተካሄደ በሚገኘው የቡድን 7 ሀገራት ስብሰባ ላይ ታድመው የነበሩት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ስብሰባውን አቋርጠው ወደ ሃገራቸው የተመለሱ ሲሆን፣ ሁኔታው ከእስራኤል እና ኢራን የተኩስ አቁም ጋር አይገናኝም ብለዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በጉባኤው፣ አሜሪካ በእስራኤል-ኢራን ጉዳይ የተኩስ አቁም ንድፈ ሀሳብ እንዳቀረበች ከገለጹ በኋላ ነው፡፡
ትራምፕ አያይዘውም ወደ ዋሽንግተን የሚያቀኑት ለምን እንደሆነ ማክሮን እንደማያውቁ በመግለጽ፣ የሳቸው ስብሰባውን አቋርጦ መውጣት ከእስራኤል-ኢራን የተኩስ አቁም ጋር እንደማይገናኝ እና ምክንያታቸው ከዛ የበለጠ እንደሆነም ነው ፕሬዚደንቱ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው በፃፉት መልዕክት የጠቆሙት፡፡
በታምራት ቢሻው