“የባህል ስፖርቶቻችንን አሳድገን አለማቀፋዊ እንዲሆኑ ማድረግ አለብን” አቶ መክዩ ሞሀመድ

You are currently viewing “የባህል ስፖርቶቻችንን አሳድገን አለማቀፋዊ እንዲሆኑ ማድረግ አለብን” አቶ መክዩ ሞሀመድ

AMN-የካቲት 29/2017 ዓ.ም

22ኛው የባህል ስፖርቶች ውድድር እና 18ኛው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫልን አስመልክቶ የማህበረሰብ አቀፍ የአካልብቃት እንቅስቃሴ ተደረገ።

ውድድሩ እና ፌስቲቫሉ በሚደረግበት ሆሳዕና ከተማ በተከናወነው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ መክዩ መሐመድ እና የባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ሕይወት መሐመድን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

አቶ መክዩ ሞሀመድ “የባህል ስፖርቶቻችን አሳድገን አለማቀፋዊ ተቀባይነት እንዲኖራቸው መስራት ይገባናል” ብለዋል። ሚኒስቴር ዴኤታው”በርካታ ዘመናዊ ስፖርቶች መነሻቸው የባህል ስፖርት በመሆኑ እኛም ጠንክረን ከሰራን የራሳችንን የባህል ስፖርት ማሳደግ እንችላለን።” ሲሉ ተናግረዋል።

በአብዬ ኤርሳሞ መታሰቢያ ስታዲየም በተከናወነው የአካል ብቃት እንቅስቀሴ በርካታ የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

“ባህላዊ ስፖርቶቻችን ለጠንካራ ህብረ-ብሔራዊ አንድነታችን” በሚል መሪ ሃሳብ የሚደረገው 22ኛው የባህል ስፖርቶች ውድድር እና 18ኛው የባህል ስፖርት ፌስቲቫል ዛሬ በድምቀት ይጀምራል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሆሳዕና ከተማ ላይ በሚደረገው በዚህ የባህል ስፖርት እና ፌስቲቫል 1,386 ስፖርተኞች በ11 የስፖርት ዓይነት ይሳተፋሉ።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review