የባህልና ስፖርት ዘርፍ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በፖለቲካ እንዲሁም በዲፕሎማሲው ዘርፍ ዋና አንቀሳቃሽና የኢትዮጵያን ገፅታ የሚቀይር ነው፦ ቋሚ ኮሚቴው

You are currently viewing የባህልና ስፖርት ዘርፍ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በፖለቲካ እንዲሁም በዲፕሎማሲው ዘርፍ ዋና አንቀሳቃሽና የኢትዮጵያን ገፅታ የሚቀይር ነው፦ ቋሚ ኮሚቴው

AMN – ጥር 9/2017 ዓ.ም

የጤና ማህበራዊ ጉዳዮች ባህልና ስፖርት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወርቀሰሙ ማሞ የተመራ ልዑክ አደይ አበባና አዲስ አበባ ስታዲዮም ላይ ምልከታ አድርጓል።

የቋሚ ኮሚቴው አባላት ፕሮጀክቱን ተዘዋውረው ምልከታ በማድረግ የግንባታ ሂደቱን ገምግመዋል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወርቀሰሙ ማሞ እንደገለጹት፣ የባህልና ስፖርት ዘርፍ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በፖለቲካ እንዲሁም በዲፕሎማሲው ዘርፍ ዋና አንቀሳቃሽና የኢትዮጵያን ገፅታ የሚቀይር ነው።

ዘርፉ የኢትዮጵያን ከፍታ የሚያሳይ አብሮነትንና ወንድማማችንን የሚያመጣ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

ፕሮጀክቱ እንዲፈጥን እና አመራሩ የበለጠ ክትትል እንዲያደርግ አሳስበዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ ቋሚ ኮሚቴው ስለሚያደርገው እገዛ አመስግነው፤ ፕሮጀክቱን በተለየ ሁኔታ በመከታተል ውጤት እንዲያመጣ እየተጋን ነው ብለዋል።

የቋሚ ኮሚቴው አባላት ማብራሪያ የሚፈልጉ ጉዳዮችን አንስተው ከተቋራጩ ምላሽ ተሰጥቶባቸው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ፕሮጀክቱ የካፍ (CAF) እና የፊፋ (FIFA) ስታንዳርድ ጠብቆ እየተሰራ እንደሚገኝ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review