የብሄራዊ ቤተመንግሥት ሙዚየም ከዛሬ ጀምሮ ለሕዝብ እይታ ክፍት መሆኑን ተገለጸ

You are currently viewing የብሄራዊ ቤተመንግሥት ሙዚየም ከዛሬ ጀምሮ ለሕዝብ እይታ ክፍት መሆኑን ተገለጸ

AMN ሰኔ 10/2017 ዓ.ም

የብሄራዊ ቤተመንግሥት ሙዚየም ከዛሬ ጀምሮ ለሕዝብ እይታ ክፍት መሆኑን በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የቤተመንግሥት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ምትኩ ዴሬሳ ገለፁ።

ለአራት ወራት የሙከራ አገልግሎት ላይ የነበረው የብሄራዊ ቤተመንግሥት ሙዚየም ከዛሬ ጀምሮ ለሕዝብ እይታ ክፍት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከ ጠዋቱ ከ 3፡00 ሠዓት ጀምሮ እስከ ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ማንኛውም ሰው አገልግሎት ማግኘት ይቻላል ፣ ከ11፡30 ሰዓት እስከ ምሽት 3፡00 ሰዓት ድረስ ቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ አገልግሎትን ማግኘትና መጎብኘት እንደሚቻል ዋና አስተዳደሪው ገልጸዋል።

የለውጡ መንግስት ባለፉት 7 አመታት በቱሪዝም ልማት ዘርፍ በርካታ ጉልህ ስራዎችን ስለ መስራቱም አንስተዋል፡፡

ዋና ዋና የሚጎበኙት ቅርሶች የመኪና ሙዚየም ፣ ዋናው ብሄራዊ የብሄራዊ ለቤተመንግሥት ፣ ውድ የሆኑ እና ለብዙ ዘመናት ተጠብቆ የኖረ ቅርስ እና ሌሎችም ቅርሶች ይጎበኛሉ ብለዋል።

ደረጃውን የጠበቀ ካፍቴሪያ አገልግሎት ጨምሮ ሌሎች የመዝናኛ አማራጮች መኖራቸዉም ተገልጿል፡፡

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review