የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ ሰው ተኮር እና የሪፎርም ስራዎችን እየጎበኙ ነው

You are currently viewing የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ ሰው ተኮር እና የሪፎርም ስራዎችን እየጎበኙ ነው

AMN – ጥር 22/2017 ዓ.ም

ከጥር 23 አስከ 25 የሚካሄደው የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ ሰው ተኮር እና የሪፎርም ስራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ ባስጀመሩት ጉብኝት በአዲስአበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የተሰሩ የሪፎርም ስራዎች እየተጎበኙ ነው።

የአዲስ አበባ መሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ጌታቸው በመሬት ልማት ዙሪያ የተሰሩ የሪፎርም ስራዎችን ለጉባኤው ተሳታፊዎች ባብራሩበት ወቅት እንዳሉት በሪፎርሙ ተቋሙን ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ በማሻገር ከብልሹ አሰራር ጋር ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን ማስቀረት ተችሏል።

በቢሮው በሪፎርም የተሰሩ ስራዎችን የጎበኙት የብልጽግና ጉባኤ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ያገኙትን ተሞክሮ ወደ መጡበት ሲመለሱ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰሩ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ተናግረዋል።

በአሸናፊ በላይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review