የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጎልቤ ሲሌ ፣ ከብልፅግና ፓርቲ የመጀመሪያ ጉባኤ በኋላ በክልሉ ስለተመዘገቡ ማህበራዊ ስኬቶች ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፤

You are currently viewing የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጎልቤ ሲሌ ፣ ከብልፅግና ፓርቲ የመጀመሪያ ጉባኤ በኋላ በክልሉ ስለተመዘገቡ ማህበራዊ ስኬቶች ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፤

-በአፋር ክልል በጤናው ዘርፍ ቀደም ሲል የነበረውን መከላከል ላይ ያተኮረ እንቅስቃሴ አሁን ህክምናም ተጨምሮበት አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል፤

-በክልሉ ከሦስት ዓመት በፊት ሦስት ሆስፒታሎች ከነበሩበት አሁን የሆስፒታሎች ቁጥር ጨምሯል፣ በጤና ጣቢያ ደረጃ የነበሩ ማስፋፊያ ተደርጎላቸው ወደ ሆስፒታል ደረጃ እንዲያድጉም ተሰርቷል፤

-የመድሃኒት፣ የጤና፣ የአምቡላንስ፣ የጤና ኬላ እና የጤና ጣቢያ ተደራሽነት በየአካባቢው ሽፋኑን ፊት ከነበረው የማሳደግ እና የማዳረስ ሥራ ተሰርቷል፤

-በጤናው ዘርፍ ከተሰራው የተደራሽነት ሥራ ባለፈ በጤና ቁሳቁስ አቅርቦት እና የአገልግሎት ጥራት ላይም ሰፊ ስራ ተሰርቷል፤

-በጤናው ዘርፍ በጣም አመርቂ ውጤት የተገኘበት ሌላኛው ጉዳይ የጤና መድህን አገልግሎት ሲሆን፣ ወረዳዎችን አቅፎ ወደተግባር ከመግባት አኳያ በልዩ ትኩረት በመሰራቱ የክልሉን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ከማድረግ አንፃር ይበል የሚያሰኝ ውጤት ሊመዘገብበት ችሏል፤

-የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ ረገድ የሚቀሩ ጉዳዮች ቢኖሩም፤ በመምህራን፣ በተማሪዎች፣ በወላጆች እና በአጠቃላይ በትምህርት ከባቢ በተሰሩ የማሻሻያ ሥራዎች አበረታች ውጤት ተመዝግቧል፤

AMN- ጥር 21/2017 ዓ.ም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review