የብርቱካን ያልሆነው የብርቱካን ታሪክ ወይም የልበ ወለዷ ብርቱካን ታሪክ የድህረ እውነት ፖለቲካ ትልቅ ማሳያ ነው – ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

You are currently viewing የብርቱካን ያልሆነው የብርቱካን ታሪክ ወይም የልበ ወለዷ ብርቱካን ታሪክ የድህረ እውነት ፖለቲካ ትልቅ ማሳያ ነው – ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

AMN – ሚያዝያ 03/2017

የኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባስተላለፉት መልዕክት የብርቱካን ያልሆነው የብርቱካን ታሪክ ወይም የልበ ወለዷ ብርቱካን ታሪክ የድህረ እውነት ፖለቲካ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።

ሰዎች ከሀቅ ከእውነተኛ መረጃ እና ማስረጃ ይልቅ ይሁነኝ ተብሎ በሚቀነባበሩ፣ ሀሰተኛ የሆኑ ግን በቀላሉ ስሜት በሚቀሳቅሱ፣ በተዛቡ እና በተሳሳቱ መረጃዎች ምን ያህል እንደሚሸወዱ፣ ባለሰቡትና ባልገመቱት መንገድ የእኩይ ወይም የሴራ ፖለቲካ ሰለባ እንደሚሆኑ የሚያመለክት ነው ብለዋል።

ሃብት ንብረቶቻቸውን ጭምር በይሆናል ተነሳስተው ለሴራ ፖለቲካ አቀናባሪዎች ሲሳይ እንደሚሆኑ ጭምር የሚያሳይ ነው።

የድርሰቱ አቀናበሪዎች “ህዝብን በቀላሉ በማጃጃል ለተፈለገው ዓላማ ማሰለፍ ይቻላል” የሚለውን ኋላቀር የአክራሪነት አስተሳሰብ መሠረት አድርገው ላልተሰካ የፖለቲካ ትርፍ ተንቀሳቅሰዋል ብለዋል።

ለነገሩማ የቡርቱካን፣ የሮዝ ወዘተ የቀለም አብዮት ጠንሳሾች ምሁራንን፣ ፖለቲካኞችን፣ ባላሃብቶችን፣ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ልሂቃኖችን፣ የሚዲያ ሰዎች፣ ዳያስፖራውን፣ ማህበራዊ አንቂዎችን ወዘተ በመጠቀም ይሁነኝ ተብለው በተቀነባበሩ ሀሰተኛ ስሜት ቀስቃሽ መረጃዎች በመጠቀም መንግስታትን አፍርሰዋል።

በእርዳታ አቅርቦት፣ በፕራይቬታይዜሽን፣ በብድር የየሀገሮቹን ሀብቶች ዘርፈዋል።

ሀገሮቹም በግጭት አዙሪት እንዲዳክሩ አድርገዋል።

እናም የብርቱካን ያልሆነው የብርቱካን ታሪክ በተለያዩ ጊዜያት ኢትዮጵያን የማተራመስ፣ በግጭት አዙሪት የማቆየት፣ በህዝቦች መካካል የማይበርድ እሳት ለማቀጣጠል በሀሰተኛ መረጃ ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ ሴራ ነው ብለዋል።

እንዲህ አይነቶቹ የፈጠራ ድራማዎች በየቀኑና በየሰዓቱ በማህበራዊ ሚዲያም ሆነ በመደበኛው በአንዳንድ ጽንፋኛ ሚዲያዎች ይፈበረካሉ።

የሰፋውን የዲሞክራሲ ምህዳር ተጠቅመው በጠራራ ፀሐይ ውሸት ሲፈበርኩ ህግ ይከበር ሲባል በስሜት ቀስቃሽ የሀሰተኛ ዲራማዎች ለእኩይ ሴራዎቻቸው በዘረጉት ኔት ወርክ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላሉ።

ህዝቡንም ጥርጣሬ ውስጥ ለመክታት ይሞክራሉ።

ደግነቱ ህዝባችን አመዛዛኝ ነው፣ እነሱ እንደሚሉት በቀላሉ የሚጀጃል አይደለም።

ነገሮችን በርጋታ ማየት ልምድ አዳብሯል። የዚያኑ ያህል ደግሞ በክፈት ሴራው ሰለባ የሚሆነው ቀላል ቁጥር ያለው አይደለም።

ይህ አጋጣሚ ለሚዲያዎቻችንም ሆነ ለማህበረሰቡም ጥሩ ትምህርት የሚሰጥ ነው። ስለሆነም ቆም ብሎ ከዚህ መማር ብልህነት ነው ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review