የቬይትናም ጠቅላይ ሚኒስተር ክቡር ፋም ሚን ቺን በይፋዊ ጉብኝታችን ወቅት ላደረጉልን የደመቀ አቀባበል እና የክብር መስተንግዶ አመሰግናለሁ። ኢትዮጵያና ቬይትናም የሚያመሳስሏቸው ብዙ የጋራ ጉዳዮች አሏቸው። ሁለታችንም ትልቅ እና ለሥራ የተነሳሳ ወጣት ሕዝብ ያለን፣ ለልማት እና እድገት የቆረጠ‍ን እንዲሁም በታሪካችን ሂደትም በፅናታችን የምንታወቅ ሀገራት ነን።

You are currently viewing የቬይትናም ጠቅላይ ሚኒስተር ክቡር ፋም ሚን ቺን በይፋዊ ጉብኝታችን ወቅት ላደረጉልን የደመቀ አቀባበል እና የክብር መስተንግዶ አመሰግናለሁ። ኢትዮጵያና ቬይትናም የሚያመሳስሏቸው ብዙ የጋራ ጉዳዮች አሏቸው። ሁለታችንም ትልቅ እና ለሥራ የተነሳሳ ወጣት ሕዝብ ያለን፣ ለልማት እና እድገት የቆረጠ‍ን እንዲሁም በታሪካችን ሂደትም በፅናታችን የምንታወቅ ሀገራት ነን።

ውይይታችን በንቁ ተሳትፎ የሚገለጥ እና ጥልቀትም የነበረው ነበር።

ለጋራ እድገት እና ትብብር ያለንን ፅኑ የጋራ ተነሳሽነትም አንፀባርቀናል። የሃሳብ ልውውጣችን በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ለጠንካራ ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር በር ከፍቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ፋም ሚን ቺን በቅርብ ኢትዮጵያን በሚጎበኙበት ወቅት የጋራ ርዕዮቻችንን የበለጠ የምናጠናክርበት እና በዛሬው የአለማችን አውድ የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ይበልጥ የምናፀናበት ይሆናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review