
AMN – ጥር 5/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የጥምቀት በዓል በሰላምና በአብሮነት ተከብሮ እንዲውል ከማዕከል እስከ ወረዳ ካሉት የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባቶች ጋር የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው።
በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ ባለፉት ጊዜያት በህዝብ እና መንግስት የጋራ ጥረት የተለያዩ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ ሆኗል ብለዋል።
በቀጣይ የሚከበረው የጥምቀት በዓል በድምቀት እንዲከበር መንግስት የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛልም ብለዋል።
ለዚህም ይረዳ ዘንድ የተለያዩ ህዝባዊ ውይይቶች እየተካሄዱ መሆኑም ተገልጿል።
በዓሉ ባማረ መልኩ ተከብሮ እንዲውል ሁሉም ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት እንዳለበትም ተመላክቷል።
በሀብታሙ ሙለታ