የተለያዩ አገራት ሚኒስትሮችና ባለስልጣናት አህጉር አቀፍ የሰላም ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ

AMN ህዳር 16/2017 ዓ .ም

“የበለፀገችና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ” በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ በሚጀመረው አህጉር አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ ለመሳተፍ የደቡብ አፍሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ሞትሸክጋ ማትሴ እና የልዑካን ቡድናቸው አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ሚኒስትሩ አዲስ አበባ ሲደርሱ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) እና የሰላም ሚኒስቴር አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

“የበለፀገችና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ” በሚል መሪ ሃሳብ አሁጉር አቀፍ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል ዛሬ ያካሂዳል።

ኮንፈረንሱ ለሀገራችን የገፅታ ግንባታ ከሚጫወተው ሚና በተጨማሪ አገራችን የራሷን የሰላም ቁርጠኝነትና ልምድ ለሌሎች የአፍሪካ ሃገራት የምታጋራበት መድረክ እንደሆነም ተመላክቷል፡፡

በኮንፈረሱ ለመሳተፍ የርዋንዳ ፣ቡርንዲ ፣ላይበሪያ ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች አዲስ አበባ መግባታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review