AMN-ጥር 22/2017 ዓ.ም
የተርክዬ ኤኬ ፓርቲ እና የሞሮኮው ናሽናል ራሊ ኦፍ ኢንዲፔንደንትስ(አር ኤን አይ) ፓርቲ አመራሮች በብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ለመታደም አዲስ አበባ ገቡ።
የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባዔው ላይ የሚታደሙ የውጭ ሀገራት የገዥ ፓርቲ ተወካዮች አዲስ አበባ እየገቡ ነው።
በዚህም የተርክዬው ኤኬ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ዛፈር ሲራካያ እና የሞሮኮው ‘ናሽናል ራሊ ኢንዲፔንደንትስ'(አር ኤን አይ) ፖርቲ ተወካይ መሐመድ ሳዲኪ አዲስ አበባ ገብተዋል።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር)፣ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለእንግዶቹ አቀባበል አድርገውላቸዋል።