የተፈታታ የፒክአኘ ተሽከርካሪ አካል በከሰል ጭነት ዉስጥ በመሸሸግ ከዳንግላ ከተማ ወደ ባህርዳር ከተማ ሲያጓጉዙ የነበሩ ግለሰቦች በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጀጃው ሞላ (ኢ/ር) ተናግረዋል፡፡
ግለሰቦቹ ጽንፈኛ ቡድኑ የዘረፋትን ፒክአኘ ተሽከርካሪ የውስጥ አካል በመፍታት ወደ ባህርዳር ከተማ ወስደው ለመሸጥ በመጓዝ ላይ የነበሩ ቢሆንም በህብረተሰቡ ጥቆማ ሊያዙ ችለዋል፡፡
ከከሰል ጋር ቀላቅለው በመጫን የወንጀሉ ተባባሪ የሆኑት አሽከርካሪው እና ረዳቱ 60 ሺህ ብር እንደተከፈላቸው ያረጋገጠው ፖሊስ፣ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ከአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡