የተሸከርካሪዎችን ፍጥነት ለመቆጣጠር ልዩ የትራፊክ መስመሮችን ያስተዋወቀችው ከተማ

You are currently viewing የተሸከርካሪዎችን ፍጥነት ለመቆጣጠር ልዩ የትራፊክ መስመሮችን ያስተዋወቀችው ከተማ

AMN – መጋቢት 29/2017 ዓ.ም

በአሜሪካ ፔንሲልቫኒያ ግዛት በሞንትጎመሪ ከተማ፣ ባለስልጣናት የተሸከርካሪዎችን ፍጥነት ለመቀነስ በሚል ጠመዝማዛ የመንገድ መስመሮችን አስተዋውቀዋል፡፡

አሁን በዚህች ከተማ ግራጫውን የአስፓልት መልክ ተከትሎ ማሽከርከር ለመጀመሪያ ጊዜ ጉዞን ዝግ የሚያደርግ ሆኗል፡፡

ይህ የሆነበት ምክንያትም መደበኞቹ የመስመር ንድፎች በሰካራም የተቀቡ መስለው በሚታዩ ጠመዝማዛ መስመሮች ስለተተኩ ነው።

እንደ ሞንትጎሜሪ ከተማ ባለሥልጣናት ገለፃ፣ ይህ ያልተለመደ ንድፍ በአንዳንድ የማዘጋጃ ቤቱ ጎዳናዎች ላይ በፍጥነት መጓዝን ለመከላከል ከሁሉ የተሻለ መፍትሔ እንደሆነ ተጠቁሟል።

ይህ የማስተካከያ እርምጃ፣ አንዳንድ መንገዶች እንደ “ፍጥነት መንገድ” እየታዩ እንዳለ በመግለፅ ለሚቀርቡ በርካታ ቅሬታዎች ምላሽ ለመስጠት መወሰዱን የፖሊስ ምንጮች ገልጸዋል።

ሞንትጎሜሪ ከተማ ፖሊስ በፌስቡክ ገፃቸው፣ “የአውራ ጎዳና ደህንነት መሐንዲሶቻችን እና የትራፊክ መሐንዲሶቻችን ይህ የአካባቢውን ነዋሪዎች ደህንነት ለመጠበቅ ከሁሉ የተሻለ እርምጃ እንደሆነ ወስነዋል” በማለት ጽፈዋል።

በአካባቢው ፍጥነትን ለመቆጣጠር በርካታ ሙከራዎች ተደርገው አመርቂ ውጤት እንዳላመጡ የገለጹት ባለሥልጣናቱ፣ እነዚህ ጠመዝማዛ መስሮች ከሁሉም የተሸለ አማራጭ ተደርገው መወሰዳቸውን አክለዋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ውሳኔው በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ መሆኑን የኦዲቲ ሴንትራል ዘገባ ያመለክታል፡፡

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review