
AMN – ህዳር 3/2017 ዓ.ም
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑ አስፈጻሚ አካላትን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም፣ ዛሬ መገምገም መጀመሩን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ በተቋም ግንባታ ማዕቀፍ በተሠራዉ ሪፎርም በርካታ የሀገር ሀብት ከሚባክንበትና በየዓመቱ ኪሣራ ከሚመዘገብበት ታሪክ መዉጣት ተችሏል ብለዋል።
በዚህም የሀገርን ኢኮኖሚ የሚደግፉ እና በቢሊዮኖች የሚቆጠር ብር በየዓመቱ ትርፍ የሚያስመዝግቡ፣ ለበርካቶች የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ፣ ለዕዉቀት እና ለቴክኖሎጂ ሽግግር አስተዋጽዖ የሚያበረክቱ ተቋማትን ፈጥረናልም ነው ያሉት፡፡
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ በሆኑ ሁሉም ተቋማት የተጀመረዉ ሪፎርም ባለፉት ዓመታት የሚለካና የሚቆጠር ዉጤት አምጥቷል ሲሉም ገልጸዋል፡፡
በዛሬዉ መድረክ በዋናነት በመጀመሪያዉ ሩብ የበጀት ዓመት ለማሳካት ካቀድናቸዉ ጉዳዮች ዉስጥ ዋና ዋና አፈጻጸሞችን እንገመግማለን ሲሉም አክለዋል፡፡
በመሆኑም በተገቢው መንገድ ያሳካናቸዉን በማየት በጉድለት የታዩትንም በመንቀስ ፣ ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮ