የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ስለ አፍሪካ ምን አሉ?

You are currently viewing የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ስለ አፍሪካ ምን አሉ?

• አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና እና ተገቢውን ፍትህ እንድታገኝ ከአፍሪካ ህብረት እና ከሁሉም አባል ሀገራት ጋር በጋራ እንሰራለን

• አፍሪካ የሚታይ ተስፋ ያላት አህጉር ናት

የቅኝ ግዛት ዘመን ጠባሳ ዛሬም ድረስ አፍሪካን እና አፍሪካውያንን እየጎዳ ነው፣ አፍሪካ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል አለመሆኗ በቂ ማሳያ ነው

• በአፍሪካ አንዳንድ አካባቢዎች የፀጥታ ችግሮች መኖራቸው አሳሳቢ ነው፣ ችግሮችን በመሳሪያ ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ በመመካከር እና በመነጋገር መፍታት ይገባል

• አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለደረሰባት ችግር ፍትህ ልታገኝ ይገባል

• አፍሪካ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ሁለት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት የሚደረገው እንቅስቃሴ ይቀጥላል

• በተመድ እና በአፍሪካ ኅብረት መካከል ያለው ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል

• በሱዳን፣ በኮንጎ፣ በሶማሊያ በመካከለኛው ምሥራቅ እና በሌሎችም አገራት ግጭት እና ቀጠናዊ ውጥረት መቆም አለበት።

• ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔን በመስጠት በሱዳን፣ በኮንጎ እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ያሉ ግጭቶች በፍጥነት አፍሪካዊ መፍትሔ ማግኘት አለባቸው

• አፍሪካ ለነፃነቷ ያደረገችውን ጥረት አደንቃለሁ፣በቀጣይም ኢ-ፍትሐዊነት ተወግዶ ወደ ትክክለኛ ዕድገቷ እንደምትሄድ እምነት አለኝ

በወርቅነህ አቢዩ

AMN-የካቲት 9/2017 ዓ.ም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review