የተባበሩት አረብ ኤምሬቶቹ ሪች ዲጂታል በኢትዮጵያ የአይሲቲ ዘርፍ መዋዕለ ንዋዩን የማፍሰስ ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

You are currently viewing የተባበሩት አረብ ኤምሬቶቹ ሪች ዲጂታል በኢትዮጵያ የአይሲቲ ዘርፍ መዋዕለ ንዋዩን የማፍሰስ ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

AMN – ጥር 5/2017 ዓ.ም

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽንና ቴክኖሎጂ ተቋም ሪች ዲጂታል በኢትዮጵያ በዘርፉ መዋዕለ ንዋዩን የማፍሰስ ጠንካራ ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ገሰሰ (ዶ/ር) ከሪች ዲጂታል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት ኮሚሽነሩ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽንና ቴክኖሎጂ ጨምሮ ኢትዮጵያ በተለያዩ ቁልፍ ዘርፎች ያላትን ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጨ አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የግሉ ዘርፍ በሀገሪቷ ኢኮኖሚ ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ ሪፎርሞችን እያደረገ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

የአይሲቲውን ዘርፍ የሚያሳድጉ ጠንካራ የፖሊሲ ማዕቀፎች መኖራቸውን የገለጹት ኮሚሽነሩ፥ፖሊሲው መንግስት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትምንት ለመሳብ እየተገበራቸው ከሚገኙ ኢኒሼቲቮች ጋር የተቆራኘ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ክህሎት ያለው የሰው ኃይል፣ ኢነርጂ፣ ኢንተርኔት እና የአይሲቲ ፓርኮችን ጨምሮ የመሰረተ ልማቶች አቅርቦት እንዲሁ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የገበያ አቅም እንዳላት አስረድተዋል።

ሪች ዲጂታል ምቹ እድሎቹን በመጠቀም በዘርፉ እንዲሰማራ ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽንና ቴክኖሎጂ ተቋም ሪች ዲጂታል (REACH Digital) ተወካዮች በበኩላቸው ተቋሙ በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋዩን የማፍሰስ ጠንካራ ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ለአይሲቲ ልማት አመቺ ምህዳር እንዳለ መናገራቸውን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review