የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋው በደረሰበት ቦታ ተገኝተው የተመለከቱ ሲሆን፣ በሆስፒታል ያሉ የተጎጂ ቤተሰቦችንም አፅናንተዋል፡፡
በሀዘን ላይ የሚገኙ የተጎጂ ቤተሰቦችም በመንግስት በኩል ስለ አደጋው የሚሰጥ መረጃ ካለ በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡
በትናንትናው እለት 242 ሰዎችን አሳፍሮ ከህንድ ወደ ለንደን በረራ የጀመረው አውሮፕላን እስከ አሁን ድረስ ምክንያቱ ባልታወቀ ዕክል በመኖሪያ መንደር ላይ ወድቆ ከአንድ ሰው በስተቀር የሁሉም መንገደኛ ሕይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡
ይሁንና አውሮፕላኑ በወደቀበት የመኖሪያ ህንፃ አካባቢ የሞቱ ሰዎች ቁጥር በውል አለመታወቁን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የተጎጂ ቤተሰቦችም በህይወት ያጧቸውን ወዳጅ ዘመድ መለየት የሚያስችል የዲኤንኤ ምርመራ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
በማሬ ቃጦ