የታላቁ ብሄራዊ ቤተ መንግስት የዕድሳት ስራ ተጠናቅቆ ለጎብኚዎች ክፍት ይሆናል

You are currently viewing የታላቁ ብሄራዊ ቤተ መንግስት የዕድሳት ስራ ተጠናቅቆ ለጎብኚዎች ክፍት ይሆናል

AMN-ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም

የብሔራዊ ቤተ መንግስቱ የዕድስት ስራ ያለበትን ደረጃ፣ሂደቱን እና ቀሪ ስራዎችን በተመለከተ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ወ/ሮ አለምፀኃይ ጳውሎስ ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ለተሰባሰቡ የሚዲያ አመራሮች አስጎብኝተዋል።

አብዛኛው የዕድሳት ስራ ወደ መገባደድ ምዕራፍ ላይ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሯ ለዕድሳቱ ያስፈልግ የነበረውን ፋይናንስ በማገዝ በኩል ቀደም ብሎ ታድሶ ለጎብኚዎች ክፍት የሆነው የአንድነት ፓርክ ከፍተኛውን አስተዋፅዖ ማበርከቱን ጠቅሰዋል።

የብሔራዊ ቤተ መንግስቱ የዕድስት ስራ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅም ለጎብኚዎች ክፍት ይሆናል ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review