የትምህርት ተቋማት የሀገሪቷ ምሶሶ እና በማህበረሰቡ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ በመሆናቸው ችግሮችን በውይይት የሚፈታ ዜጋ ማምረት እንዳለባቸው የህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሃይለየሱስ ታየ ተናገሩ።
“ፌዴራሊዝም፣ህብረ-ብሄራዊ ፌዴራሊዝም፣ሀገረ መንግስት ግንባታ እና የትምህርት ተቋማት ሚና ” በሚል ርዕስ ለትምህርት ተቋማት አመራሮች፣ባለሙያዎች እና መምህራን የተዘጋጀ የአሰልጣኞች ስልጠና እየተካሄደ ነው።
በስልጠናውም የፌዴራሊዝም ጽንሰ ሀሳብ እና በጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ ድርሻ ውስጥ የትምህርት ተቋማትና ባለሙያዎችን ሚና በተመለከተ ጥናታዊ ጽሁፎች በተለያዩ ባለሙያዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
ስልጠናውን ያስጀመሩት የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሃይለየሱስ ታየ ፣በምክንያት የሚያምንና ችግሮችን በውይይት መፍታት የሚችል ዜጋን በማነጽ የትምህርት ተቋማት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ከባለሙያዎቹ ብዙ ይጠበቃል ብለዋል።
በዓለሙ ኢላላ