የትራምፕን የ104 በመቶ ታሪፍ መጨመርን ተከትሎ ቻይና አጸፋዊ ምላሽ ሰጠች

You are currently viewing የትራምፕን የ104 በመቶ ታሪፍ መጨመርን ተከትሎ ቻይና አጸፋዊ ምላሽ ሰጠች

AMN -ሚያዝያ1/2017 ዓ.ም

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጣሉትን የ104 በመቶ ታሪፍ ተከትሎ፣ ቻይና ከአሜሪካ ወደ ሃገሯ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ84 በመቶ ታሪፍ መጣሏን አስታወቀች።

በሁለቱ ሃያላን እና የባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ ሃገሮች መካከል ያለው የንግድ ጦርነት እየተባባሰ መሄዱን እየወጡ ያሉ መረጃዎች ያመላከልታሉ።

ከ11 በመቶ ጀምሮ እስካ 104 በመቶ የደረሰው የታሪፍ መጠን፣ አሁን በ60 የአሜሪካ የንግድ አጋሮች ወደ አሜሪካ በሚመጡ ምርቶች ላይ መጣሉ ተገልጿል።

ትራምፕ አዲሱን ታሪፍ ካወጁ በኋላ የዓለማችን ገበያዎች በትሪሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት ሲገለጽ፣ ብዙ አሜሪካዊያን ደግሞ የዋጋ ንረት ስጋት ውስጥ እንደጣላቸው ተመልክቷል።

አሜሪካ የ104 ታሪፍ መጣሏን ተከትሎ፣ ቤጂንግ 34 በመቶ የነበረውን በአሜሪካ ምርቶች ላይ የጣለችውን ታሪፍ ወደ 84 በመቶ በማሳደግ ፈጣን ምላሽ መስጠቷን ከቢቢሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review