የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በመላው ዓለም እየተከበረ ነው፡፡
ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ክርስቲያኖች የትንሣኤን በዓል በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች እያከበሩ ይገኛሉ።
በዓሉን አስመልክቶ የግሪክ ሰማይ በርችቶች ሲያሸበርቅ፤ኢየሱስ ክርስቶስ በተሰቀለባት በኢየሩሳሌም የሚገኙ አማኞች ደግሞ በዓሉን ሻማ በማብራትና በተለያዩ ኃይማኖታዊ ስነስርዓቶች እያከበሩ ይገኛሉ፡፡
በሀገራችን ኢትዮጵያም በዓሉ በተለያዩ መንፈሳዊ ስነስርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡
የተለያዩ ሀገራት የትንሳኤ በዓልን እንዴት እያከበሩት ነው ሲል ቢቢሲ የሚከተለውን መረጃ በምስል አጋርቷል፡፡