ከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት በጾም በጸሎት ያሳለፉ አቅመ ደካሞችን ፣ አካል ጉዳተኞች እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች የተጋለጡ ወገኖችን በአብሮሆት ቤተመፃፍት ማስፈሰካቸውን ገልፀዋል።
በባህላችን መሰረት ሌሎች በየቤታቸዉ በለሊት ፆም ሲፈቱ እና በዓሉን በድምቀት ሲያከብሩ ጠያቂ የሌላቸው አረጋውያን ፣ የሀገር ባለዉለታዎች እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ወገኖች የጾሙን ወቅት በጾም እና በጸሎት አሳልፈው በፍቺው ጊዜ ባይተዋርነት እንዳይሰማቸው ሁሌም የከተማ አስተዳደሩ እንደማይዘነጋቸውም ከንቲባ አዳነች ጠቅሰው፤ ዛሬም እነዚህ ወገኖች ፆም እንዲፈቱ አድርገናል ብለዋል።