AMN-ጥር 22/2017 ዓ.ም
ሊቀመንበሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ፣ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ኢፋ ሙለታ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
በጉባዔው ከ15 ሀገራት የተውጣጡ የጎረቤት ሀገራት እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች 43 ከፍተኛ አመራሮች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡