AMN-ጥር 22/2017 ዓ.ም
የአልጄሪያ ብሔራዊ ነፃነት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ ፕሮፌሰር አብደልከሪም ቤን መባረክ የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመታደም አዲስ አበባ ገብተዋል።
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ” ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሐሳብ ከጥር 23 እስከ 25 በአዲስ አበባ ያካሂዳል።