የአማራ ክልል ሕዝብ ጥያቄ የመሠረተ ልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የልማት እና በድምሩ የመበልፀግ ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing የአማራ ክልል ሕዝብ ጥያቄ የመሠረተ ልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የልማት እና በድምሩ የመበልፀግ ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN – የካቲት 8/2017 ዓ.ም

አሁን የአማራ ክልል ሕዝብ ጥያቄ የመሠረተ ልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የልማት እና በድምሩ የመበልፀግ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፣ “እውነትና ንጋት እንደሚባለው በሀሰት ፕሮፓጋንዳ እውነትን በማዛባት ህዝብን በዘላቂነት እያደናገሩ መቆየት እንደማይቻል የአማራ ክልል ምክር ቤት የሰሞኑ የውይይት ድባብ ጥሩ ማሳያ ነው” ብለዋል።

“ገቢር ነበብ ማለት እንዲህ ነው፤ ትናንትን ትመረምራለህ፤ ዛሬን ትገመግማለህ። ነገን ትተነብያለህ። መሬት ላይ ባለው ወሳኝ መረጃ ላይ ተመስርተህ ትክክለኛውን መንገድ መከተል የማይቀር ሀቅ ነው” ሲሉም ነው የገለጹት።

አሁን የአማራ ክልል ሕዝብ ጥያቄ የመሠረተ ልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የልማት እና በድምሩ የመበልፀግ መሆኑንም ጠቁመዋል።

“እኛም ሰምተናል የህዝባችንን ጥያቄዎች ከህዝባችን ጋር ሆነን ምላሽ ለመስጠት እንደሁሌው እንተጋለን” ሲሉም አስፍረዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review