የአማራ ክልል አምራች ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ከፍተኛ መነቃቃትን አሳይቷል- ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing የአማራ ክልል አምራች ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ከፍተኛ መነቃቃትን አሳይቷል- ተመስገን ጥሩነህ

AMN – የካቲት 26/2017 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በክልሉ በነበራቸው ቆይታ የአማራ ብረታብረት ኢንዱስትሪ እና ማሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኢንተርፕራይዝን የስራ ሂደት መመልከታቸውን ገልጸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ኢንተርፕራይዙ በተሰማራባቸው የብረት ማቅለጥ፣ የማሽነሪ ምርት፣ የኮሪደር ዲች ከቨሮች፣ ስማርት ፖሎች፣ የትራንስፎርመር እና የእርሻ መሣሪያዎችን በመገጣጠም ለክልሉ የልማት ስራዎች መፋጠን ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል፡፡

በተለይም ተኪ ምርቶችን ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሪን ከማዳን ባለፈ የልማት ስራዎች በግብዓት እጥረት እንዳይስተጓጎሉ እያገዘ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

አምራቾች ለተኪ ምርት ትኩረት በመስጠት ሀገራዊ ግብ እንዲሳካ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review