የአንድ አመራር ብቃት የሚለካዉ በቂ ተኪዎችን በማዘጋጀትና በመፍጠር አቅሙ ጭምር ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
በበቂ ሁኔታ ተተኪ ማፍራት ካልተቻለ የአመራር መዛነፍ፣ የጉዞ መደነቃቀፍ ያጋጥማል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መንግስት በርከት ያሉ ወጣቶችን በፖለቲካ ውስጥ አስገብቶ እና አሰልጥኖ እንዲሁም ስራ ሰጥቶ እንዲለማመዱ አስችሏል ብለዋል።
መሪነት በእውቀት ብቻ ሳይሆን በችሎታ እና በጥበብም ጭምር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እሳቸው በሚመሩት ካቢኔ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ወጣት ስለመሆኑ አመላክተዋል።
እየተሰራ ካለው ስራ አንፃር ለወደፊት ኢትዮጵያን ማን ይረከባታል የሚለው ጉዳይ አያሰጋንም ሲሉም አክለው ተናግረዋል።
በሊያት ካሳሁን