የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የሰጠውን ከቀረጥ ነጻ የገበያ ዕድል በአግባቡ መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ውይይት ተካሄደ

May be an image of 8 people and text

AMN ህዳር 19/2017 ዓ.ም

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የሰጠውን ከኮታ እና ከቀረጥ ነጻ የገበያ ዕድል በአግባቡ መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

መድረኩ በአውሮፓ ህብረት የአካባቢን ዘላቂ ጠቀሜታ እውን ለማድረግ እየተተገበሩ ያሉ የሕግ ማዕቀፎች ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ አልባሳት በሚያመርቱ ኩባንያዎች ላይ የሚሳድረው ተጽዕኖ ላይ ያተኮረ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የአውሮፓ ህብረት የአካባቢን ዘላቂ ጠቀሜታ እውን ለማድረግ እየተገበራቸው ያሉ የሕግ ማዕቀፎች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ተመርተው ወደ ህብረቱ ገበያ የሚቀርቡ አልባሳት ከአከባቢ ጋር ተስማሚ እንዲሆኑ እንደሚያስገድድም ተገልጿል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ፓርኮች ውስጥ ያሉ ባለሃብቶች ለዓለም ገበያ የሚያቀርቧቸው ምርቶች ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት የአልባሳት ውጤቶች መሆናቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

All reactions:

4949

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review