የአውሮፓ ህብረት ላቀረባቸው ጥያቄዎች ከሃገራችን ዘላቂ ጥቅም አንጻር የተቃኙ ምላሾችን ሰጥተናል – ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

You are currently viewing የአውሮፓ ህብረት ላቀረባቸው ጥያቄዎች ከሃገራችን ዘላቂ ጥቅም አንጻር የተቃኙ ምላሾችን ሰጥተናል – ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

AMN – መጋቢት 8/2017 ዓ.ም

ለ5ኛው የአለም ንግድ ድርጅት የሥራ ላይ ቡድን ስብሰባ፣ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ የሚገኘው የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን፣ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ጋር የሁለትዮሽ የገበያ እድል ድርድርን የተመለከተ ስብሰባ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት እንደገለጹት፣ የአውሮፓ ህብረት ላቀረባቸው ጥያቄች ከሃገራችን ዘላቂ ጥቅም አንጻር የተቃኙ ምላሾችን ሰጥተናል ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም፣ በሚቀጥለው ረቡዕ በሚካሄድው የአለም ንግድ ድርጅት አባልነት ስብሰባ ጎን ለጎን፣ ከሃገራት ጋር የሚኖረን የሁለትዮሽ ስብሰባዎችን ማድረግ እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review