የአየር ንብረት ለውጥ በሎስ አንጀለስ የተከሰተው ሰደድ እሳት እንዲባባስ ምክንያት መሆኑ ተነገረ

You are currently viewing የአየር ንብረት ለውጥ በሎስ አንጀለስ የተከሰተው ሰደድ እሳት እንዲባባስ ምክንያት መሆኑ ተነገረ

AMN- ጥር 21/2017 ዓ.ም

በሎስ አንጀለስ በሞቃታማ እና ደረቅማ ንፋስ ምክንያት ለተከሰተው ሰደድ እሳት መባባስ መንስኤው የአየር ንብረት ለውጥ መሆኑን ተመራማሪዎቸ ገልጸዋል።

በአካባቢው ያለውን ሞቃታማ የአየር ሁኔታ ለማቀዝቀዝ የሚረዳ የዝናብ ሁኔታ ባለመኖሩ የሰደድ እሳቱ ሊረዝም እንደሚችል ተነግሯል፡፡

ተመራማሪዎቹ ሰደድ እሳቶቹ በጣም ውስብስብ መሆናቸውን እና ለዚህም የአየር ንብረት ለውጥ ደግሞ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በጥር ወር መጀመሪያ ላይ በተከሰተው እና በፍጥነት እየተዛመተ በቀጠለው በአውዳሚው ሰደድ እሳት ወደ 30 የሚጠጉ ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ከ10 ሺ በላይ ቤቶች መውደማቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

ነዳጅ፣ ጋዝና የድንጋይ ከሰል በስፋት ጥቅም ላይ መዋል በቢሊዮን ቶን የሚቆጠሩ የሙቀት አማቂ ጋዞች ወደ ከባቢ አየር እንዲገቡ አድርጓል። እነዚህ ጋዞች የምድርን የሙቀት መጠን በ 1 ነጥበ 5 ሴልሽየስ ከፍ እንዲል አድርገዋል።

በፈረንጆቹ 2015 በተደረሰው የፓሪስ ስምምነት የዓለም የሙቀት መጠን ከ1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች እንዲሆን ጥረት ለማድረግ ሀገራት ተስማምተው እንደነበር ይታወሳል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review