AMN – የካቲት 10/2017
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት ሁለተኛው የኮሪደር ልማት ሥራ ያለበትን ደረጃ በዛሬው ዕለት ምልከታ ያደርጋሉ።
የምክር ቤት አባላቱ ከእንጦጦ ጀምሮ እስከ ፒኮክ ድረስ ያለው ሁለተኛው የኮሪደር ልማት ሥራ ያለበትን አሁናዊ ሁኔታ የሚገመግም ይሆናል።
ጉብኝቱ ከእንጦጦ፣ አፍንጮ በር፣ ፒኮክ የወንዝ ዳርቻ የኮሪደር ልማትን የሚያጠቃልል ነው፡፡
በተጨማሪም የፒያሳ ዙሪያ ልማትን እንዲሁም ጉለሌ የተቀናጀ የልማት መንደርን፣ የካዛንቺስ አካባቢን መልሶ ማልማት ፕሮጀክትን፣ የግንፍሌ-ቀበና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጨምሮ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ በክፍለ ከተማ አቅም የተሰራ የአረንጔዴ እና መንገድ ዳርቻ ማስዋብን እንደሚያካትት ታውቋል።
በወርቅነህ አቢዮ