ድጋፉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ እና የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ መሰረት ማቲዎስ ተረክበዋል።
ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ፣ የምክር ቤቱ አባላት ወደ ጋምቤላ መምጣታቸው የአዲስ አበባ ምክር ቤት ከጋምቤላ ክልል ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክር ነው ብለዋል።
የተደረገው ድጋፍ ለተማሪዎች ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ጠቁመው የጋራ መደጋገፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር፣ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደገለፁት የተደረገው ድጋፍ ዴስክ ቶፕ እና ኮምፒውተርን ጨምሮ የመማሪያ መፅሐፍት እና ሌሎች ቁሳቁሶች እንደሚገኙበት ጠቁመዋል።
በቀጣይም ሌሎች ድጋፎችን እንደሚያደርጉ ገልጸው፣ ምክር ቤቱ ከጋምቤላ ክልል ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ማረጋገጣቸውን ከጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።