የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ አመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሄዷል፡፡
በስብሰባው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
እንዲሁም ምክር ቤቱ ከ11 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት አጽድቋል፡፡
የአዲስ አበባ ምክር ቤት ለተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች በሽግሽግ እና በአዲስ የተለያዩ ሹመቶችንም አጽድቋል፡፡
በዚህም፡-
1ኛ/ ወይዘሮ ቆንጂት ደበላ ኦላ- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
2ኛ/ አቶ አወሌ መሐመድ ኡመር -የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ
3ኛ/ ወይዘሮ አይሻ መሐመድ አደም- የአዲስ አበባ ከተማ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር
4ኛ/ ኢ/ር ሕይወት ሳሙኤል ጸጋዬ- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ እና ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር
5. ሲ/ር ሶፊያ አለሙ – የሴቶች፣ የወጣቶችና ህፃናት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል::
s