የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የአደረጃጀት አሰራርና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ ተሻሻለ
AMN-ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በዛሬ ውሎው በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አደረጃጀት አሰራርና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ አዋጅ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።

አዋጁ የምክር ቤቱን አሰራርና አደረጃጀት ለማሻሻልና የምክር ቤት አባላት ህዝብ የጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ያስችላል ተብሎ እንደታመነበት ተገልጿል፡፡
በመሆኑም የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አደረጃጀት የአሰራርና የአባላት ሥኑምግባር ደንብ በምክር ቤት አባላት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!