የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ኛ ዓመት 12ኛ መደበኛ ስብሰባዉን በሁለት ወሳኝ ከተማ አቀፍ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ኛ ዓመት 12ኛ መደበኛ ስብሰባዉን በሁለት ወሳኝ ከተማ አቀፍ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል

AMN – ሰኔ 09/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ኛ ዓመት 12ኛ መደበኛ ስብሰባዉን በሁለት ወሳኝ ከተማ አቀፍ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል ::

በዚህም መሰረት ፤-

1ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም በጀት 350 ቢሊየን ብር ሆኖ ለምክር ቤት እንዲቀርብ ፤ ውሳኔ አሳልፏል።

ረቂቅ በጀቱ በዋናነት ደህነት ቅነሳ ላይ በማትኮር ለዘላቂ ልማት፣ የስራ እድል ለሚፈጥሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶች እና ከከተማው ነዋሪ በተለያየ መንገድ ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለሚሰጡ አገልግሎትና አቅርቦት ድጎማዎችን አካቶ ካፒታል በጀት 249.9 ቢሊዮን ብር እንዲሁም ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ቁጠባን መሰረት ላደረገ የመደበኛ በጀት ደግሞ 100.1 ቢሊዮን ብር የበጀት ጣሪያ ወስኗል፡፡

2ኛ. በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ተጠንቶ በቀረበዉ የመሬት ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ ዋጋ ላይም ተወያይቶ በኮሪደር ልማት በለሙ አካባቢዎች የመሠረተ ልማት አቅርቦት ደረጃ ከፍ በማለቱ እና የኮሪደር ልማቱ በከተማ ዉስጥ የነበረዉን የመሬት ዋጋ ከመረጋጋት አንፃር እና የቀጣይ የከተማዋን የመልማት ፍላጎት በማጥናት የቀረበውን የመሬት ሊዝ ዋጋ ማሻሻያ ማፅደቁን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review