የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በ10ኛ መደበኛ ስብሰባው በ3 አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
AMN-ሚያዚያ 09/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ተኛ አመት 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን በ3 አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም መሰረት፤-
1ኛ. ተቋርጦ የነበረዉ የመኖርያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት አገልግሎትን ለማስቀጠል ተጠንቶ የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ የመልካም አስተዳደር ጥያቄን ሊፈታ በሚችል አግባብ የውሳኔ ሀሳብ አሳልፏል።

2ኛ. የብርሃን አይሰውራን፣ የመነን እና የገላን ቦርዲንግ ት/ቤቶች ካላቸው ልዩ ስምሪት፣ የጥራት ደረጃ እና ከሚያንቀሳቅሱት ሀብትና ንብረት አስተዳደር አንፃር ህጋዊ ሰውነት ኖሯቸው እንዲተዳደሩ እና ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለከተማዉ ትምህርት ቢሮ እንዲሆን የቀረበዉን ደንብ መርምሮ አጽድቋል::
3ኛ. ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ፕሮጀክቶች የቀረበ የመሬት ማስፋፊያ ጥያቄዎች ላይ ተወያይቶ ተገቢነት ያለዉ መሆኑን በማረጋገጥ ማጽደቁን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል::