የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎችን ህይወት በዘላቂነት ለመቀየር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ፡-ወንድሙ ሴታ (ኢንጂነር)

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎችን ህይወት በዘላቂነት ለመቀየር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ፡-ወንድሙ ሴታ (ኢንጂነር)

AMN – ታኅሣሥ 28/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎችን ህይወት በዘላቂነት ለመቀየር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወንድሙ ሴታ (ኢንጂነር) ተናገሩ።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ 38 ሺህ በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ወገኖች ማእድ ያጋራ ሲሆን 141 የአባወራ እና እማወራ ቤቶች በሙሉ እና በከፊል እድሳት ተደርጎላቸው ለአቅመ ደካሞች እና ለሀገር ባለውለታዎች ተላልፈዋል።

‎በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወንድሙ ሴታ (ኢንጂነር) በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ዜጎች በዓል በመጣ ቁጥር ማዕድ በማጋራት የምንረዳው ሳይሆን በዘላቂነት ኑሯቸውን መቀየር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ለዚህም በከተማዋ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

በተለይም ከተማ አስተዳደሩ የሰውን ህይወት የሚቀይሩ ሰው ተኮር ስራዎችን መሆኑን ተናግረው በተለይም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች በበዓል ወቅት ተደስተው እንዲውሉ እየተደረገ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያዊያን ያለው ለሌለው በመስጠት የሚያደርጉት የመረዳዳት ባህል በፊትም የነበረ መሆኑን ያነሱት ኢንጂነር ወንድሙ ይህ የመረዳዳት ባህል ተጠናክሮ ቀጥሎ ባህል እየሆነ መጥቷል ብለዋል።

መንግስት የጀመረው የኮሪደር ልማት ሲጠናቀቅ ለህዝቡ ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥር ነው ያሉት ዋና ስራ አስኪያጁ በክፍለ ከተማው እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማትም የክፍለ ከተማው ነዋሪም በልማት ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመዋል።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ካባ መብራቱ “በጎነት ለማህበረሰብ ለውጥ” በሚል መሪ ቃል በክፍለ ከተማው በ13ቱም ወረዳዎች እንዲሁም በተለያዩ ቀና ሃሳብ ያላቸው የእምነት ተቋማት እና ድርጅቶች ከ38 ሺህ በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ወገኖች ማእድ የማጋራት ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

‎ከዚህ በተጨማሪ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከ83 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ በሚገመት ወጪ 141 የአባወራ እና እማወራ ቤቶችን በሙሉ እና በከፊል እድሳት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች እና ለሀገር ባለውለታዎች ተላልፈዋል ሲሉ ተናግረዋል።

‎በዚህም ከ746 በላይ ሰዎችን ንፁህ መጠለያ እንዲኖራቸው ማድረግ የተቻለ ሲሆን ይህ በጎ ተግባር የብዙዎችን አቅመ ደካሞች ችግር በመቅረፍ በህዝባችን ዘንድ አብሮነትን የበለጠ የሚያጠናክር እና የጀመርነውን የብልፅግና የልማት ጉዞ የሚያጠናክር ነው ሲሉም አብራርተዋል፡፡‎

በተደረገላቸው ድጋፍ እንደተደሰቱ የገለጹት ማዕድ ተጋሪዎች ድጋፉ በዓልን በደስታ እንዲያሳልፉ እንደሚያስችላቸው ገልፀዋል።

ክፍለ ከተማው በልማት ምክንያት ወደ ሌላ ቦታ ለተዘዋወሩ ዜጎችም ማዕድ ያጋራ ሲሆን ለጸጥታ አካላትም ለቅርጫ የሚሆን ሰንጋ አበርክቷል።

በሄለን ጀንበሬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review