የአዲስ አበባ ከተማና ጋምቤላ ክልል ምክር ቤቶች ልምድ ተለዋወጡ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማና ጋምቤላ ክልል ምክር ቤቶች ልምድ ተለዋወጡ

AMN – ሚያዝያ 3/2017

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት እና የጋምቤላ ክልል ምክር ቤቶች የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ መሰረት ማቲዎስ እንደገለፁት የክልሉ ምክርቤት ከአዲስ አበባ ምክር ቤት ያገኘውን በጎ ልምድ ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈ- ጉባኤ ወይዘሪት ፋኢዛ መሀመድ በበኩላቸው የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆን የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት በጋራ ይሰራል ብለዋል።

መልካም ጎኖችን አጠናክሮ ማስቀጠል የሚያስችል የልምድ ልውውጥ መደረጉን ከክልሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review