የአፋር ፌደራላዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን ለአፋር ክልል መንግሥት አስረከቡ

AMN – ኅዳር 06/2017 ዓ.ም

የአፋር ፌደራላዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን ለአፋር ክልል መንግሥት ከክልሉ ሰላም እና ልማት በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል።

በአፋር ክልል አብአላ ከተማ ላይ በተካሄደው ሥነ-ሥርዓት ላይ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ትጥቃቸውን አስረክበው በሰላም ወደ ክልሉ ለመጡ ወጣቶች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋክ።

በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልእክት ሰላም የሁሉም ነገር መሠረት መሆኑን በመጠቆም ታጣቂዎቹ የሰላምን መንገድ መምረጣቸው ለክልሉ ሰላም መረጋገጥ ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ባሻገር ለሀገራዊ ሰላም እና አንድነት ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም በክልሉ ሰላም እና ልማት ላይ በንቃት መሳተፍ እንዲችሉ ክልሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ ስምምነቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦም ምስጋና አቅርበዋል።

ብርጋዲየር ጄኔራል ጀማል ሻሌ በበኩላቸው የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ ከዚህ ቀደምም በጋምቤላ እና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችም ትጥቃቸውን አስረክበው ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ መደረጉን አውስተዋል።

በአፋር ክልልም ትጥቅ ይዘው ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ጋር ተከታታይ ውይይቶችን በማድረግ ከአፋር ፌደራላዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ ታጣቂዎች በተጨማሪ ራሱን የአፋር ነፃ አውጪ ግንባር እያለ ከሚጠራው ታጣቂ ኃይል ጋርም በተሠራው ውጤታማ ስራ ወደ ሰላማዊ መንገድ ማምጣት እንደተቻለ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ብርጋዲየር ጄኔራል ጀማል በአሁኑ ወቅት በአፋር ክልል በሕገ ወጥ መንገድ ትጥቅ ይዞ የሚንቀሳቀስ የተደራጀ ኃይል እንደሌለ አስታውቀው ከዚህ ለሀገር አንድነት እና ሰላም ከሚበጅ በጎ ተግባር ሌሎች ክልሎችም ትምህርት ሊወስዱ ይገባል ብለዋል።

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊ ጋዶ ሐሞሎ ታጣቂዎቹን ወደ ሰላማዊ መንገድ ለማምጣት ተከታታይ ውይይቶች ሲካሔዱ መቆየታቸውን ገልጸው የሀሳብ ልዩነቶችን በሠለጠነ መንገድ መፍታት እንደ ባህል መለመድ ያለበት አሰራር ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ከግጭት እና ጦርነት የሚገኝ ትርፍ እንደሌለ የተናገሩት የአፋር ፌደራላዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ ታጣቂዎች ሊቀመንበር ሀጂ ስዩም አወል ከአሁን በኋላ ህገ መንግስታዊ ስርአቱን አክብረን በሠላማዊ መንገድ ህዝባችንን ለማገልገል በወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ካሉ በኋላ ለዚህ ታሪካዊ የሰላም ስምምነት መሳካት መከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ ላበረከተው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review