የአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ በቀጣናዊ ሰላምና መረጋጋት ዙሪያ ያላቸውን የጋራ ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለጹ

You are currently viewing የአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ በቀጣናዊ ሰላምና መረጋጋት ዙሪያ ያላቸውን የጋራ ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለጹ

AMN – መጋቢት 18/2017

የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ በቀጣናዊ ሰላም እና መረጋጋት ዙሪያ ያላቸውን የጋራ ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ በአፍሪካ ህብረት የአሜሪካ አምባሳደር ስቴፋን ሱሊቫን ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።

ውይይቱ የአፍሪካ ህብረት እና የአሜሪካ የቆየ ትብብር ማጠናከር እና አዳዲስ የትብብር መስኮችን መለየት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ነው።

የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ አጋርነት ለሶማሊያ የሰላም እና መረጋጋት ጥረቶች ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ እንዳለው አመልክተዋል።

ለቀጣናዊ ሰላም እና መረጋጋት በቁርጠኝነት መስራታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለጻቸውን ከአፍሪካ ህብረት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review