የአፍሪካ ሕብረት ችግሮች ከመከሰታቸው አስቀድሞ በመገንዘብ ጥበብ የተሞላበት አመራር መስጠት እንደሚገባ ተገለጸ

You are currently viewing የአፍሪካ ሕብረት ችግሮች ከመከሰታቸው አስቀድሞ በመገንዘብ ጥበብ የተሞላበት አመራር መስጠት እንደሚገባ ተገለጸ

AMN – ሚያዚያ 07/2017 ዓ.ም

የአፍሪካ ሕብረት የአስፈጻሚ ምክር ቤት 24ኛው አስቸኳይ ስብሰባውን በአዲስ አበባ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡

በስብሰባው ላይ በአፍሪካ ሕብረት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ሒሩት ዘመነ ባደረጉት ንግግር፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በጂኦፖለቲካ ውጥረቶች፣ ግጭትች፣ በብድር እዳ፣ በሰብአዊ ቀውሶች እና ሌሎች አይገመቴ ሁኔታዎች በአሕጉሪቷ ላይ ተፅዕኖ እንዳያሳርፉ የአፍሪካ ሕብረት ችግሮች ከመከሰታቸው አስቀድሞ በመገንዘብ ጥበብ የተሞላበት አመራር መስጠት እንዳለበት ገልጸዋል።

እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ሕብረቱ ካስቀመጠው አጀንዳ 2063 ጋር የተናበበ እና አሕጉሪቱን የተረጋጋች እና ሰላማዊ የእድገት አቅጣጫ የሚመራ መሆን እንዳለበት አብራርተዋል።

ምክር ቤቱ በስብስባው የአንድ የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ደህንነት ምክር ቤት አባል ምርጫ የሚያካሂድ ሲሆን፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የኢኮኖሚ ልማት፣ ቱሪዝም፣ ንግድ፣ ኢንዱስትሪ እና ማዕድን ኮሚሽን እና የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኮሚሽነር የምርጫ ሂደት አስመልክቶ የተዘጋጀ ረቂቅ ሪፖርትን እንደሚያዳምጥ መገለጹን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review